Skip to main content

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የክልሉ መንግስት በአዲስ መልክ ሲቋቋም የክልሉ የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 ዓ/ም መሠረት በአዲስ መልክ ከተቋቋሙ የክልል ተቋማት መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ቢሮው በአዲስ መልክ ሲደራጅ በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን፣ ክልላዊ መግባባትና አንድነትን ማጠናከር፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ዘመናዊ የፀጥታ መረጃ ፍሰት እንዲኖር ማስቻል፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጥናትና ክትትል ማድረግ፣ በክልሉ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በተለያዩ ኃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በትብብር መሰራትን ያካትታል።

ቢሮዉ ሲደራጅ በስሩ ሶስት ዋና ዋና ዘርፎችን ይዞ የተዋቀረ በመሆኑ እነዚህም፡- የግጭት አፈታትና የህግ ጉዳዮች ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ፤ የፀጥታ መረጃ አሰባሰብ፣ አቅርቦት፣ አስተዳደርና ምላሽ አሰጣጥ ዘርፍ እና የሰላም ግንባታና ብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ ሲሆን በስሩ አስራ አንድ ዋናና ደጋፊ ዳይሬክቶሬቶችን በመያዝ ተደራጅቷል። 

እንደ ቢሮ ሶስት ተጠሪ ተቋማትን ለአብነት ፖሊስ ኮሚሽን፣ ሚሊሻ ጽ/ቤት እና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲን በበላይነት የማስተባበር ኃላፊነት ተሰጥቶታል።