እንኳን ወደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኦፊሴላዊ ድህረ ገፅ በደህና መጡ!

bureau_head

እንኳን ወደ  ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በደህና መጡ!

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሰላምና ፀጥታ ቢሮ የክልሉ መንግስት በአዲስ መልክ ሲቋቋም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 199/2015 ዓ/ም መሠረት በአዲስ መልክ የተቋቋሙ የክልል ተቋማት መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ቢሮው በአዲስ መልክ ሲደራጅ በክልሉ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም ማስፈን፣ ክልላዊ መግባባትና አንድነትን ማጠናከር፣ የህግ የበላይነትን ማስከበር፣ ዘመናዊ የፀጥታ መረጃ ፍሰት እንዲኖር፣ በክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ጥናትና ክትትል ማድረግ፣ በክልሉ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እንዲሁም በተለያዩ ኃይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል ሰላምና መከባበር እንዲሰፍን ከሚመለከታቸው መንግስታዊ፣ መንግስታዊ ካልሆኑ አካላት ጋር በትብብር መሰራትን ያካትታል፡፡
በዚህ ድህረ ገፅ ላይ ቢሮዉ ሰላምን በማፅናትና የህዝቡን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ በመገንባት የሰላሙ ባለቤት ህዝቡ እንዲሆን በማስቻል የቢሮዉ የረጅም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ እቅደችን በማዘጋጀትና አጠቃላይ የሰላም እና ደህንነትን በማረጋገጥና በቴክኖሎጂ በማስተሳሰር ማእቀፎችን በመፍጠርና በመተግበር ረገድ ትልቅ ሚና በመወጣት ላይ ይገኛል፡፡ Read more

Our vision, Mission and values

             🎯 ተልዕኮ

  • በክልሉ የሰላም ባህል በመገንባት፣ የህግ የበላይነትን በማስከበር ክልላዊ መግባባትን በማጎልበት በክልሉ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን፤
  • በጥናትና ምርምር አዳዲስ የአሰራር ስልት በመቀየስ በክልል ደረጃ ወጥና ዘመናዊ የመረጃ ቅብብሎሽ ሥርዓትን መገንባት ነው::

             👁️ ራዕይ

  • "በ2022 ዓ.ም የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር፣ የህዝቡ ሠላም፣ ፀጥታና ደህንነት የተረጋገጠበት ክልል ሆኖ ማየት፤"

             💎 ዕሴት

ታማኝነት
አሳታፊነት
አገልጋይነት
ብዝሃነት
ፍትሃዊነት
ሰብአዊነት
ተግባራዊነት
አካታችነት
ሚስጥራዊነት
ህዝባዊነት