AdminPeace
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ከቡር አቶ ተመስገን ካሳ በክልሉ በህበረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የፖሊስ ጽ/ቤት ማዕከላትን ጎብኝተዋል። ሰኔ 27/2018 ዓ.ም ሆሳዕና በቢሮዉ ኃላፊ የተመራ የፀጥታ መዋቅር በከምባታ፣ በሀዲያ እና በሀላባ ዞኖች በህበረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ የፖሊስ ጽ/ቤት ማዕከላትን ጎብኝተዋል።
የቢሮዉ ኃላፊ በሶስቱም ዞኖች የስራ እንቅስቃሴና በአካባቢዎቹ ያለዉን ወቅታዊ ነባራዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ የሚያተኩር የጋራ የፀጥታ ጥምረት የግምገማ መድረክ በዱራሜ ከተማ አካሂደዋል ።
በጉብኝቱ ወቅት የክልሉ ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ ፣ የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እና የወንጀል እና ትራፍክ አደጋ መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አብርሃም ቲርካሶ፣ የክልሉ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ኮሎኔል ተሻለ ኤርዲዶ ጨምሮ የከምባታ፣ የሀዲያ እና የሀላባ ዞኖች የፀጥታ ኃላፊዎች የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የፖሊስ አዛዦች እና የአዋሳኝ ወረዳ የፀጥታ አካላት ተገኝተዋል።