Skip to main content

በፀጥታ መረጃ አሰባሰብ፣ አቅርቦት፣ አስተዳደርና ምላሽ አሰጣጥ ዘርፍ የሚሰጡ ዋና ዋና ተግባራት

 

                       ዋና ዋና ተግባራት

  • ዕቅድ ማዘጋጀትና የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረብ
  • የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
  • የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የስልጠና ሰነዶችን አዘጋጅቶ ለሚመለከተዉ አካል ተደራሽ ማድረግ
  • ሥልጠናዎችን የመስጠትና የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ግንዛቤ ማስጨበጥ
  • አካባቢያዊ የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ አመላካቾችን በጥናት በመለየት፣ መቅረጽና መከታተል፣
  • የፀጥታ ስጋት ሁኔታ ጥናት ማካሄድ
  • የግጭት ቅድመ-ማስጠንቀቂያ መረጃና ፈጣን ምላሽ አደረጃጀቶችን ማደራጀትና ማጠናከር፣
  • የስጋት መስኮችን፣ ቀጠናዎችንና የመረጃ ምንጮችን መለየት፤ ተባባሪ መመልመል፣ ስልቶችን መዘርጋትና ተልዕኮ መስጠት፣

                       ዋና ዋና ተግባራት

  • የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ከአስተዳደራዊ፣ ከመገኛኛ ብዙኃን፣ ከሰላምና ፀጥታ፣ ከኢኮኖሚ፣ ከተፈጥሮ ሀብት አጠቃምና ከማህበራዊ ሁኔታ ላይ ማሰባሰብ፣ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ፣ መተንተን እና ማሰራጨት፣
  • የፀጥታ መረጃ መሰብሰብ፣ መተንተንና ማደራጀት፣
  • የተደራጁ ወንጀሎችንና ህገ-ወጥ ድርጊቶች ላይ በልዩ ተልዕኮ በስውር ክትትል የማድረግ፣ መረጃ የመሰብሰብ እና ጥቅም ላይ እንዲዉል ማድረግ፣
  • ግጭትን ለመከላከልና ለማስቆም በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ መረጃ መሠረት ፈጣን ምላሽ መስጠትና ማስተባበር፣
  • በግጭት አዝማሚያ መነሻነት የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን አጣርቶና ትክክለኛነቱን አረጋግጦ መረጃን ከመፍትሄ ሀሳብ ጋር ለሚመለከተዉ አካል ማስተላለፍ፣

                        ዋና ዋና ተግባራት

  • መረጃዎችን በመረጃ ቋት ለመያዝ የሚያስችል የመረጃ ቴክኖሎጂ አሰራር ስርዓት መዘርጋት፣ መረጃዎችን ማደራጀትና ማስተዳደር፣
  • የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ዑደት እና ፈጣን ምላሽ ማስተባበር፣ አፈጻጸሙ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
  • የህግ ማዕቀፎችና የአሰራር ስርዓቶች የማዘጋጀትና መተግበራቸውን መከታተልና መደገፍ፣
  • መሰረታዊ መረጃ መሰብሰብ፣ ማጠናቀርና ማደራጀት፣
  • መልካም ተሞክሮን መቀመርና ማስፋት
  • የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ
  • ክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረመልስ መስጠት፣