Skip to main content

የሰላም ግንባታና ብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ በውስጡ ሁለት ዳይሬክቶሬቶች ያሉት ሲሆን የሚሰጡትም አገልግሎቶች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 

        በሰላም እሴት ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ተግባራት               

  • የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ፤
  • የህብረተሰቡን በሰላም አብሮ የመኖርና አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህልን የማጎልበት፣
  • የአሰራር ስርዓትና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀት አገልግሎት፣
  • በሰላም ግንባታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችን፣ ሴሚናሮችንና ወርክሾፖችን ማዘጋጀት፤
  • ቀጣይነት ያለው የማህበረሰብ ተኮር የምክክር መድረኮችን የማመቻቸትና የማስተባብር፣
  • የሰላም እሴትን የማስረጽና የማጎልበት አገልግሎት፣
  • የንቅናቄ መድረኮችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በሰላም ዙሪያ በባለቤትነት እንዲሰለፉ የማድረግ፣
  • ማናቸውም የልማትና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎች ሰላምን የሚያጎለብቱና የግጭት ተጋላጭነትን የሚቀንሱ መሆናቸውን የመከታተል፣
  • የሰላም አደረጃጀቶችን በማህበረሰቡና በትምህርት ተቋማት የማደራጅትና የማጠናክር፣
  • የህብረተሰቡን ጠቃሚ የሰላም እሴቶችንና የአኗኗር ዘይቤዎችን የማዳብር፣
  • ብሔራዊ መግባባትንና ማህበራዊ ትስስርን ለማጠናከር የብሔራዊ በጐ ፈቃድ ማህበረሰብ አገልግሎት ተሣታፊ ወጣቶችን የመመልመል፣ የማሰማራትና ክትትል የማድረግ፤
  • በህትመትና በኤሌክትሮኒክስ ሚዲያዎች የሰላም ባህል ግንባታን የማጎልበት
  • መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀትና ጥቅም ላይ የማዋል
  • ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ የመስጠት፤
  • ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ተግባራት ናቸው፡፡

በሀይማኖትና እምነት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሚከናወኑ ተግባራት

  • ሃይማኖት ነክ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን እንዲሁም የአሠራርና የአደረጃጀት ክፍተቶችን መነሻ በማድረግ፣
  • የፍላጎትና የክፍተት ዳሰሳ ጥናት ማካሄድ፤
  • የአሰራርና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀትና ለተጠቃሚ የማዳረስ፣
  • በሀይማኖትና እምነት ተቋማት እንዲሁም በተከታዮቻቸው መካከል የአብሮነት፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች እንዲዳብሩ የግንዛቤ ማስጨባጫና የሥልጠና ሥራዎችን የሚያከናውን፣
  • አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት፣
  • የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬትን በማረጋገጥ ድጋፍ መስጠት፣
  • የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማጎልበት፤ የመደገፍ፣ የማጠናከር፣የመከታተልና የማብቃት፣
  • በሀይማኖት ሽፋን የሚፈጸሙ የአክራሪነትና ጽንፈኝነት አመለካከት ችግሮች እንዳይከሰቱ የሚከላከል፣
  • የሀይማኖትና እምነት ተቋማት በህግ አግባብ እንዲመሩ የሚሰራና፣
  • የሃይማኖት ነክ መረጃዎችን የመሰብሰብ፣ የመተንተን፣ የማደራጀትና ጥቅም ላይ የማዋል አገልግሎት፣
  • ክትትል፣ ድጋፍና ግብረ መልስ መስጠት፤
  • ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ተግባራት ናቸው፡፡